Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በጅግጅጋ እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መመሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የአስፋልትና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የሚገኙበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም ከመንገድ ግንባታው ጎን ለጎን በግንባታ ላይ የሚገኘውን የከተማዋን የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ የመስመር ዝርጋታ ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ቀዚህም ወቅት ሁሉም የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ መመሪያ መስጠታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.