Fana: At a Speed of Life!

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ የከፍተኛ አመራሮቹን የሥራ መልቀቂያ አልቀበልም አለ

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ የከፍተኛ አመራሮቹን የሥራ መልቀቂያ አልቀበልም ማለቱ ተገለጸ።

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።

በስብሰባው በተለይም በፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኩል ‘‘አሁን ላሉ በርካታ ጉዳዮች ላለፉት 4 ዓመታት በከፍተኛ አመራርነት ያገለገልን አመራሮች ለቀን በአዲስ እንተካ’’ የሚለውን ሀሳብ ፓርቲው ጊዜ ሰጥቶ የተወያየበት መሆኑን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጣሂር ሞሀመድ ተናግረዋል።

ሆኖም ሊቀመንበሩ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ሀሳብ ማዕከላዊ ኮሚቴው አልቀበልም ማለቱን የዘገበው አሚኮ ነው።

‘’አሁን እየታየ ላለው ችግር የመፍትሄ አካል ለመሆንም አዳዲስ አመራሮችን ወደፊት በማምጣት እንተካካ’’ የሚለውን ሀሳብም ፓርቲው ሐምሌ 18/2014 በሚያካሂደው ስብሰባ በጥልቀት እንደሚያየውና እስከዚያም ፓርቲው በትኩረት ስራውን እየሰራ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የፓርቲው ውስጣዊ አንድነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ፓርቲው እንዴት ያያቸዋል የሚል ሀሳብ ከመገናኛ ብዙሀን ሙያተኞች የተነሳላቸው ኃላፊው ፥ ማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችና ለድርጅቱም አቅምና ውስጣዊ አንድነት የሚበጁትን ሃሳቦችና ውሳኔዎች የምናሳርፍበት ስብሰባ ሀምሌ 18 ይካሄዳል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.