Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ኀብረት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጎዴ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኀብረት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርሲክ እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ገብቷል፡፡
 
ልዑካኑ ኡጋስ ሚራድ ላይሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ ቃሲም የተመራ የልዑካን ቡድን አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ ጎቡኝት በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የድርቅ አደጋ ተጽዕኖ ሁኔታ፣ በድርቁ አደጋ የተሰጠውን ምላሽና በመካሄድ ላይ ባሉ የልማት ስራዎች ላይ የሚጫወቱትን ሚና ለመገምገም ያለመ ነው ተብሏል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ልዑካኑ ከክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት ጋር በክልሉ መሰረተ ልማት ሥራዎች ድጋፍ በሚሰጡበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.