ቴክ

ቻይና የመጀመሪያውን ሰው አልባ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን አስተዋወቀች

By Alemayehu Geremew

June 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና “ቲ ፒ 500” የተሰኘ የመጀመሪያውን ግዙፍ ሰው አልባ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን አስተዋውቃለች።

አውሮፕላኑ የተሠራው አቪየሽን ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በተሰኘው የመጀመሪያው የቻይና ሀገር በቀል ኢኒስቲትዩት ሲሆን የቻይና የበረራ አገልግሎት ደግሞ የቁጥጥር ሥራውን ማከናወኑ ነው የተመለከተው፡፡

አውሮፕላኑ የሙከራ በረራውን ጂንግሜን በተሰኘችው የቻይናዋ ሁቤይ ግዛት በሥኬት ፈጽሟል ተብሏል፡፡

ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኑ በሙከራ በረራው ለ 27 ደቂቃዎች ዓየር ላይ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ሰው አልባው ግዙፍ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ከባሕር ጠለል በላይ እስከ 1 ሺህ 800 ኪሎ ሜትር ከፍታ መብረር እንደሚችልም ነው ሲ ጂ ቲ ኤን የዘገበው፡፡

500 ኪሎ ግራም ክብደት ያለውን ጭነት ይዞ እስከ 500 ኪሎ ሜትር የመብረር አቅም እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

https://news.cgtn.com/news/2022-06-19/China-s-first-large-CCAR-TP500-unmanned-freighter-makes-maiden-flight-1aZb6TNa0FO/index.html