Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ላይ የተፈጸመው ግድያ አገራችንን ከአሸባሪዎች ለማጽዳት የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክረን ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለን ማሳያ ነው – ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አገራችንን ከአሸባሪዎች ለማጽዳት የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክረን ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለን ማሳያ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ፥ “በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሸባሪው ሸኔ በንጹሐን ወገኖች ላይ በፈጸመውን ግድያ የተሰማኝን ሀዘን እየገለጽኩ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁ” ብለዋል።

“ድርጊቱ አገራችንን ከአሸባሪዎች ለማጽዳት የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክረን ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለን ማሳያ ነው” ሲሉ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.