ዓለምአቀፋዊ ዜና

የእስራኤል ጥምር መንግስት ፓርላማውን በመበተን አስገዳጅ ምርጫ ለማድረግ ረቂቅ ሊያቀርብ ነው

By Meseret Awoke

June 21, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጥምር መንግስት ፓርላማውን በመበተን አስገዳጅ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ሊያቀርብ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያይር ላፒድ በቀጣዩ ሳምንት ረቂቁን እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።

ረቂቁ ከፀደቀም ፓርላማውን በመበተን አስገዳጅ ምርጫ ይደረጋል ነው የተባለው።

የጥምር መንግስቱ መሪዎች እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ጥምረቱን ለማረጋጋት ያስችላል ያሉትን ሁሉንም አይነት ጥረት አሟጠው ከተጠቀሙ በኋላ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ረቂቅ ህጉ ከፀደቀ ላፒድ የጊዜያዊው መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆን ኤ ኤፍ ፒን ዋቢ ያደረገው የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!