ዓለምአቀፋዊ ዜና

የኢንዶኔዢያው ፕሬዚዳንት ጆኮዊ በሩሲያና ዩክሬን ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

By Meseret Awoke

June 21, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዶኔዢያ ፕሬዚዳንት ጆኮዊ ሩሲያንና ዩክሬንን ሊጎበኙ ነው።

በጉብኝታቸው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ስንዴ ወደ ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ ለማሳመን ጥረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሩሲያ እንደሚጓዙ የዘገበው ጃካርታ ፖስት፥ ወደ ዩክሬን እና ሩሲያ ከማቅናታቸው በፊት በሚቀጥለው ሳምንት በጀርመን በሚካሄደው የቡድን 7 ስብሰባ ላይ እንደሚታደሙም አስታውሷል፡፡

በጉብኝታቸው በመጭው ህዳር ወር ኢንዶኔዢያ በምታስተናግደው የቡድን 20 አባል ሃገራት ስብሰባ ጉዳይ ላይ ከፑቲን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!