የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍ እንዲል ለማስቻል እየተሠራ ነው – አቶ መላኩ አለበል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቆዎች ለመፍታት የተጀመረው የኢትዮጰያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የአምራቾችን ችግር በመፍታት ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍ እንዲል ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “አዲስ ለልጆቿ አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ” የሚለው ፕሮጀክት፥ ተማሪዎች በትምህርት ጊዜያቸው የሚያስፈልጋቸውን መሰረታዊ የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ እንዲለብሱ በማድረግ ለትምህርት ጥራቱና ለአዕምሮ ግንባታ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታችና ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባልም ነው ያሉት አቶ መላኩ፡፡
ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ አልባሳት፥ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ማምረት አንዱ የኢትዮጵያ ታምርት ዓላማ ነው ማለታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የትምህርት ስርዓቱን በማሻሻልና ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፥ ብቁና ሀገር ወዳድ ዜጋ የሚገነባው ትምህርት ቤት ውስጥ በመሆኑ በቀዳሚነት ትምህርት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የሀገር እድገትና ኢኮኖሚ ግንባታ ከሁሉም ቀዳሚ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!