Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ችግሮችን የሚፈታ ወርቃማ እድል ነው -ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ሀገሪቱን አንድ ምዕራፍ የሚያሻግር ችግሮቿንም የሚፈታ ወርቃማ እድል ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ፍትህ መምህር ዶክተር ማርሸት ታደሰ÷ አሁን ያሉ የችግር ድሪቶዎችን ቀንሰን ነገዋ የተሻለች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኮሚሽኑ ያለበት ሃላፊነት ቀላል አይደለም ነው ያሉት፡፡

በምክክር እንዲሁም ህጋዊ መንገድ ችግሮች ይፈታሉ ብሎ የሚያስብ ማህበረሰብን ለመፍጠርም ይህ ኮሚሽን ያለበት አደራ ቀላል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

አማራጭ ሃሳቦች በሰፉ ቁጥር ነገሮች መፍትሄ ወደ ማግኘት መምጣታቸው አይቀርምና በኮሚሽኑና በህዝቡ መካከል አመኔታ እንዲጨምር ስራዎችን ማሳወቅ እና ግልፅ ማድረግ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንትፖሮሎጂ መምህሩ ዱባለ ገበየሁ በበኩላቸው÷ እገዛና ድጋፍ በማድረግ በኮሚሽኑ ለተያዙ አጀንዳዎች መሳካት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በተቃራኒ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ግን ምናልባትም እድሉን በተጠቀምንበት ወደሚል ቁጭት እና ምሬት እንዳይመልሰን ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ እንደሆነም ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡

በሀይማኖት ወንድራድ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.