ስፓርት

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

By Mikias Ayele

June 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ28ኛ ሳምንት በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ጨዋታውን ላደረገው ባህርዳር ከተማ መናፍ አወል ብቸኛዋ የማሸነፊያ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

የጣና ሞገዶቹ ዘሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 33 በማድረስ ከወራጅ ቀጠና ሸሽተዋል፡፡

 

በቀጣይ ባህር ዳር ከተማ ከሰበታ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን፥ በአንጻሩ ድሬዳዋ ከተማ ከአዳማ ከተማ እና ከፋሲል ከነማ ጋር ቀሪ ጨዋታውን ያደርጋል።