ጤና

ከፈረንጆቹ 1979 ወዲህ በስፔን የኮሌራ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተ

By Alemayehu Geremew

June 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፈረንጆቹ 1979 ወዲህ በስፔን ካስቲል-ላ ማንቻ ግዛት የኮሌራ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ ተገለጸ፡፡

አንድ ሕፃን የቧንቧ ውሃ በመጠጣቱ ምክንያት መታመሙን እና በምርመራም የኮሌራ በሽታ መሆኑ መለየቱን የግዛቲቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የበሽታውን መከሰት ተከትሎ በአካባቢው የሚገኝ አንድ የእርሻ ቦታ መዘጋቱን ነው ሲ ጂ ቲ ኤን ኤል ፓይስ የተሰኘውን ጋዜጣ ጠቅሶ የዘገበው።

በዚህ ዓመት በፈረንጆቹ ግንቦት 8 በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ ተከስቶ የአንድ ግለሰብ ሕይወት እንዳለፈና ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ በበሽታው መያዛቸው ተገልጾ ነበር፡፡