ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ ላይ ምርቶቿን አስተዋወቀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ ላይ ምርቶቿን ማስተዋወቋን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ለሦስት ቀናት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ጋልገር ስብሰባ ማዕከል በተካሄደው አውደ ርዕይ ላይ ኢትዮጵያ ቡና፣ የጥራጥሬ እና የቅመማ ቅመም ምርቶቿን በማቅረብ ለደቡብ አፍሪካ ገበያ አስተዋውቃለች።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በ19ኛው የአፍሪካ ግዙፍ 7 የምግብ እና መጠጦች ኢንዱስትሪ የንግድ አውደ-ርዕይ ላይ መሳተፉን በመረጃው ያመላከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡
አውደ-ርዕዩ ከፈረንጆቹ ሰኔ 19 እስከ ሰኔ 21 መካሄዱም ተጠቁሟል።