Fana: At a Speed of Life!

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቂያና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር አካሄደ።

በመርሐ-ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ታድመውበታል፡፡

የመርሐ ግብሩ ዓላማ የክልሉን እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮች ማስተዋወቅና ገቢ ማሰባሰብ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ÷ ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬት ፣ የተፈጥሮ ሐብት ፣ የድንጋይ ከሰል እንዲሁም ወርቅን ጨምሮ የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት የሚገኝበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ክልሉ ቡና እና ቅመማ ቅመም ለማምረትም የሚያስችል አቅም አለው ነው የተባለው፡፡

በመርሐ-ግብሩ ባለሐብቶች እና የልማት ድርጅቶች በተለያዩ ዘርፎች ላይ የማልማት ፍላጎታቸውን አሳይተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎችና የልማት ድርጅቶች ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “አብረን እንለማለን ፤ አብረን እናድጋለን፤ ክልሉን ማሳደግ አዲስ አበባን ማሳደግ ነው ምክንያቱም አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት” ብለዋል።

በሐብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.