የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ

By Melaku Gedif

June 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል እና የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሻን ካላሀን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና አጋር ድርጅቱ የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰሩ ለቆዩት የልማት ድጋፍና ደራሽ እርዳታ ምስጋና ማቅረባቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!