የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚቴው በትግራይ ክልል በግጭት ለተጎዱ 15 ሺህ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

June 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሂደውን የሰብል ምርጥ ዘር ስርጭት በመቀጠል በትግራይ ክልል በግጭቱ ለተጎዱ 15 ሺህ አርሶ አደር አባወራዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸው አርሶ አደሮች በትግራይ ክልል በላዕላይ ማይጨው ከሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች እና በማዕከላዊ ትግራይ ዞን በአድዋ ወረዳ ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች የመጡ ናቸው ተብሏል።