የሀገር ውስጥ ዜና

ጣሊያን በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

By Alemayehu Geremew

June 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጻለች፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ከጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ሉዊጂ ዲ ማዮ ጣሊያን በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት በሚያስፈልግባቸው ሥፍራዎች እንዲደርስ እና አካታች ብሔራዊ ምክክር እንዲካሄድ እያደረገች ያለውን ያላሰለሰ ጥረት ጣሊያን እንደምታደንቅ መግለጻቸውንም በኢትዮጵያ ከጣሊያን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡