የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረሪ ክልል 80 ሺህ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ እንደሚከናወን ተገለጸ

By Meseret Awoke

June 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በያዝነው ክረምት 80 ሺህ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ እንደሚከናወን የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ እንደገለጹት በሚከናወነው የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራም÷ በከተማና ገጠር ወረዳዎች የ100 አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤት እድሳት ይካሄዳል።

በተጨማሪም ወጣቶቹ የደም ልገሳ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የከተማ ግብርና እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች እንዲሳተፉ በቀረበው ጥሪ መሰረት ዝግጅት ተጠናቋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!