የአልሸባብ ከፍተኛ አዛዥ የነበረው በሽር መሃመድ ኮርጋብ በሶማሊያ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ተገደለ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የአልሸባብ ከፍተኛ አዛዥ የነበረው በሽር መሃመድ ኮርጋብ በሶማሊያ በተፈፀመ የአየር ጥቃት መገደሉ ተገለፀ፡፡
አሜሪካ በፈረንጆቹ 2008 በሽር መሀመድ ኮርጋብ የሚገኝበትን ለጠቆመ 5ሚሊየን ዶላር ሽልማት አበረክታለሁ በማለት ቃል ገብታ ነበር።
በሶማሊያ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃቶችን በተደጋጋሚ የምትፈፅምው አሜሪካ በጉዳዩ ዙሪያ እስከአሁን የሰጠቸው አስተያየት የለም።
ሆኖም የበሽር መሃመድ ኮርጋብ ቤተሰቦች ግለሰቡ መሞቱን ማረጋገጣቸው ተጠቁሟል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በደቡብ ሶማሊያ ሳኮው ግዛት የሶማሊያ ጦር እና በአሜሪካ ጦር በቅንጅት በፈፀሙት ጥቃት ግለሰቡ መገደሉን የሶማሊያ መንግስት ሬዲዮ ዘግቧል ፡፡
ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው አልሸባብ ብዙሃኑን የደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ ተቆጣጥሮ ይገኛል።
ምንጭ÷ቢቢሲ