Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሪክስ የከፍተኛ አመራሮች ዓለም አቀፍ የልማት ውይይት ላይ ተሳተፉ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በተዘጋጀው የብራዚል፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን ባካተተው የብሪክስ ፕላስ የከፍተኛ አመራሮች ዓለም አቀፍ የልማት ውይይት ላይ ተሳተፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ÷ በስብሰባው ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ፥ “እንደነዚህ ያሉት መድረኮች የጋራ ትግበራ ሲታከልባቸው፣ እንደ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የተጋፈጥናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ለመፍታት ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋሉም” ነው ያሉት።

የብሪክስ ሀገራት ትብብር በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች እንዲሁም በኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ማዕቀፎችም ጭምር መጠናከር እንዳለበትም በስብሰባው ላይ ተጠቁሟል።

የብሪክስ መሪዎች ትብብራቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር በየጊዜው መገናኘት እንዳለባቸውና በወቅታዊ ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይም የበኩላቸውን ዕልባት መሥጠት እንዳለባቸው በተለይ ከደቡብ አፍሪካ ሀሳብ ቀርቧል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተቀረጸውን የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ሀገራት ሐብታቸውን ማቀናጀት እና በትብብር መሥራት እንዳለባቸው የመሪዎቹ ጉባኤ ላይ ተጠቁሟል፡፡

14ኛውን የብሪክስ ሀገራት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በበይነ-መረብ የመሩት ሲሆን፥ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ፣ የብራዚል ፕሬዚዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ፣ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በዘንድሮው ጉባዔ ላይ ተጋባዥ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.