የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በምእራብ ወለጋና በጋምቤላ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዙ

By Feven Bishaw

June 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በምእራብ ወለጋና በጋምቤላ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘው በቀጣይ የጥቃቱን ተጎጂዎች ከመደገፍ ጎን ለጎን ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።