የሀገር ውስጥ ዜና

በጸረ-ሠላም ኃይሎች ጫና ውስጥ የነበሩ 289 ንጹሃን የጉሙዝ ተወላጆች ቡለን ወረዳ ማዕከል ገቡ

By Feven Bishaw

June 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡለን ወረዳ በዶሽና ሞች ቀበሌዎች በጸረ-ሠላም ኃይሎች ጫና ጫካ ውስጥ የነበሩ 289 ንጹሃን የጉሙዝ ተወላጆች ቡለን ከተማ ገብተዋል።

የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ ዛሬ በጸረ-ሠላም ኃይሉ ላይ በወሰዱት እርምጃ በጫና ውስጥ የነበሩ 289 ንጹሃን የጉሙዝ የማህበረሠብ ክፍሎች ከጸረ ሠላም ኃይሎች ተነጥለው ቡለን ከተማ መግባታቸው ተገልጿል፡፡