የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከጌጣጌጥ ማዕድናት ማግኘት ያለባትን እንድታገኝ ዋጋና የደረጃ ተመን ተነስቶ የንግድ ሥርዓቱ በገበያ ብቻ እንዲመራ ተወሰነ

By Feven Bishaw

June 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከጌጣጌጥ ማዕድናት ዘርፍ ማግኘት ያለባትን እንድታገኝ ከዚህ በፊት ስራ ላይ የነበረው በመንግስት የዋጋና የደረጃ ተመን ተነስቶ የንግድ ሥርዓቱ በገበያ ብቻ እንዲመራ መወሰኑን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ዑማ ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷የጌጣጌጥ ማዕድናት የግብይት ሰንሰለትን ለማቃለልና ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን እንድታገኝ ከዚህ በፊት ስራ ላይ የነበረውን በመንግስት የዋጋና የደረጃ ተመን እንዲሁም ሌሎች አላስፈላጊ መስፈርቶች ተነስተው የንግድ ሥርዓቱ በገበያ ብቻ የተመራ እንዲሆን ወስነናል ሲሉ አስፍረዋል።

በኢትዮጵያ በርካታ ማዕድናት እንደሚገኙ መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን ÷ከእነዚህ ውስጥ  ኤመረልድ፣ሳፋየርና ኦፓል  ይጠቀሳሉ፡፡