Fana: At a Speed of Life!

የምስራቃዊ ዩክሬኗ ሴቪዬሮዶኔስክ ከተማ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ከተማዋ ሴቪዬሮዶኔስክ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር መዋሏን የከተማዋ ከንቲባ ኦሌክሳንደር ሲትሩክ ገልፀዋል፡፡
ከንቲባው እንዳሉት፥ ከሳምንታት እልህ አስጨራሽ ውጊያ በኋላ የሩሲያ ወታደሮች ከተማዋን የተቆጣጠሩ ሲሆን፥ አዛዦችን በመሾም የራሳቸውን ስርዓት በመመስረት ላይ ናቸው፡፡
የሩስያ ወታደሮች ባደረጉት መጠነ ሰፊ ውጊያ የዩክሬን ተከላካይ ወታደራዊ ኃይልን ከኢንዱስትሪ ከተማዋ እንዲያፈገፍግ አስገድደዋል ሲሉም ከንቲባው ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ተደብቀው ከነበረበት የአዞት የኬሚካል ፋብሪካ ለቀው መውጣት መጀመራቸውን ተናግረዋል ከንቲባው፡፡
የሩስያ ጦር የሴቪዬሮዶኔስክ ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ሌላኛዋ የምስራቃዊ ዩክሬን ከተማ ሊቻነስክ ፊቱን እንደሚያዞር ይጠበቃል፡፡
በቀጣይ ወታደሮቹ የሊቻነስክ ከተማን የሚቆጣጠሩ ከሆነ÷ ሰፊውን የሉሀነስክ ክልል መቆጣጠር የሚያስችላቸው መሆኑን አልጀዚራ እና ሞስኮ ታይምስ ዘግበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.