Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 9 ወራት ዳያስፖራው ለልዩ ልዩ አገራዊ ጥሪዎችና ፕሮጀክቶች ያደረገው ድጋፍ ከ1 ነጥብ 37 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ ዳያስፖራው ለልዩ ልዩ ሀገራዊ ጥሪዎችና ፕሮጀክቶች ያደረገው የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ከ1 ነጥብ 37 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን መድረሱን የዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
 
በፌዴራልና በክልል ደረጃ ከሚገኙ የዳያስፖራ ባለድርሻ አካላት ጋር የ2014 በጀት ዓመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡፡
 
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ÷በመድረኩ ከዳያስፖራ ተሳትፎ አንጻር ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ መክክር መደረጉን ተናግረዋል፡፡
 
የዳያስፖራ ባለድርሻ አካላት የዳያስፖራ ተሳትፎን ለማሳደግ የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጠናከርና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለዳያስፖራው ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ዶ/ር መሐመድ አንስተዋል፡፡
 
በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ ዳያስፖራው ለልዩ ልዩ አገራዊ ጥሪዎችና ፕሮጀክቶች ያደረገው የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ከ1 ነጥብ 37 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
 
ዳያስፖራው ከሀገሩ ጋር ያለው ግንኙነት በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት በመጀመሩ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚሻገርና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድም የዳያስፖራ ማህበረሰብ እየተፈጠረ መምጣቱን ገልጸዋል።
 
የዳያስፖራውን ዕምቅ አቅም በማስተባበር ተሳትፎውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና ኢትዮጵያ ከዳያስፖራዋ የምትፈልጋቸውን ወረቶች አሟጦ ለመጠቀም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ሀላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.