Fana: At a Speed of Life!

“ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በአርባምንጭ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛው “ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በአርባ ምንጭ ከተማ ተጀምሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ÷ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ፣ የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የዛሬው “ስለኢትዮጵያ” የምክክር መድረክ በሰላም፣ ዴሞክራሲና እውነተኛ ፌደራሊዝም ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
“ስለኢትዮጵያ” መድረክ የመጀመሪያው በጅግጅጋ የተካሄደ ሲሆን፥ የተቀሩት መድረኮች በድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሀዋሳ ከተሞች መካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
በበርናባስ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.