Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ህብረተሰቡ ከስርቆት ሊጠብቀው እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም አጠናክሮ እንዲቀጥል ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ከስርቆትና ውድመት ሊጠብቀው እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በተጋረጡበት ችግሮች እና ሊወሰዱ በሚገባቸው መፍትሔዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን በርኦ በውይይቲ ላይ እንደገለጹት÷ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠውን ሀገራዊ ግልጋሎት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚፈፀምበትን ስርቆትና ውድመት ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሥራ ሊሰራ ይገባል፡፡

የክልል ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የደህንነት ተቋማት፣ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አካላት ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለመሠረተ ልማቱ ጥበቃ ሊያደርጉ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የአማራ እና ሶማሌ ክልሎች የባቡር መሠረተ ልማቱን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ከኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርትን ከስርቆትና ውድመት ለመጠበቅ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

በውይይቱ÷ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ረዳት ኮሚሽነር፣ የክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ከዞንና ወረዳ የተወጣጡ አመራሮች መሳተፋቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.