Fana: At a Speed of Life!

የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ሀገራዊ ምክክር በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የምክክር መድረኩ “የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን እየታገልን የዴሞክራሲ ስርአት እንገንባ” በሚል መሪቃል ነው እየተካሄደ ያለው።

በመድረኩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እንድሪስን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የሚሰሩ ባለሙያዎች፣ ማህበራዊ አንቂዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት በአገር ላይ የደቀነውን ጉዳት አስመልክቶ መነሻ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ቴክኖሎጂው ይዞት የመጣውን አዲስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተስማማና በተጣጣመ መልኩ ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግርን ለማረቅ መታገል ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርመሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው÷ በመሰል መድረኮች የሚንፀባረቁ ሃሳቦች በሚደረገው ትግል ውስጥ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።

በሐብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.