Fana: At a Speed of Life!

ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ፥ ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የባህል ትስስርና ጠንካራ ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት፥ ኩባ ለኢትዮጵያ ልዩ ቦታ ትሰጣለች።

የሁለትዮሽ ግንኙነት ደረጃችን በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፥ በባለብዙ ወገን መድረኮች ሁለቱ አገራት ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ነው የጠቆሙት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ፥ ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች እያበረከተች ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በተመለከተም ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.