ስፓርት

በቤልጂየም የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

By Melaku Gedif

June 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በቤልጂየም በተካሄደው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ ርቀቱን በ15 ደቂቃ14 ሰከንድ በ01 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡

ሌላኛዋ አትሌት አሳየች አይቸው ደግሞ ርቀቱን በ15 ደቂቃ በ14 ሰከንድ በ77ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌደረሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡