Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በጉጂ ዞን ለሚገነባው ነጌሌ አውሮፕላን ማረፊያ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ የተመራ ልዑክ በጉጂ ዞን ለሚገነባው ነጌሌ አውሮፕላን ማረፊያ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቆ ለመክፈት በዛሬው ዕለት ጉጂ ዞን ገብቷል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ አባላት ጉጂ ዞን ሲገቡ የዞኑ የስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አቀባባል ያደረጉላቸው መሆኑን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
እንደ ክልሉ መንግስት መረጃ በ2014 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል የከተማ ክላስተር 5 ሺህ 782 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለህዝብ ዝግጁ ተደርገዋል።
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.