Fana: At a Speed of Life!

ዩክሬን እና ሩሲያ በቁጥር ከፍተኛው ነው የተባለለትን የእስረኞች ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን እና ሩሲያ ባሳለፍነው የካቲት 24 በመካከላቸው ግጭት ከተፈጠረ አንስቶ በቁጥር ከፍተኛው ነው የተባለለትን የእስረኞች ልውውጥ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

የእስረኞች ልውውጥ ማድረጋቸውን የገለጸው የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት መሆኑም ነው የተመላከተው፡፡

በተካሄደው ልውውጥም ከ19 እስከ 65 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 144 ዩክሬናውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነግሯል፡፡

ሩሲያ ከለቀቀቻቸው እስረኞች መካከል 59 ዩክሬናውያን ወታደሮች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል 43ቱ ማሪዮፖል በተካሄደው ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል መባሉን የዘገበው ሺንዋ ነው።

ዩክሬን እና ሩሲያ የመጀመሪያውን የእስረኞች ልውውጥ ያደረጉት በዚህ ዓመት መጋቢት 24 ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.