ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኔቶ ፊንላንድን እና ስዊድንን በአባልነት ለመቀበል ወሰነ

By Alemayehu Geremew

June 30, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ፊንላንድን እና ስዊድንን በአባልነት ለመቀበል ወሰነ።

ጉባኤውን በማድሪድ እያካሄደ ያለው ኔቶ ሁለቱ ሀገራት የአባልነት ስምምነቶችን እንዲፈርሙ ጥሪ አቅርቧል።

ፊንላንድ እና ስዊድን ቃል ኪዳኑን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ቱርክ የሀገራቱን የመቀላቀል ፍላጎት ስትቃወም ብትቆይም አሁን ላይ ጥያቄዋን አንስታለች።

ሩሲያ በበኩሏ ሀገራቱ ኔቶን በመቀላቀላቸው የሚያጋጥማት ችግር እንደሌለ መግለጿን አር ቲ ዘግቧል።