Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው በተለያዩ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሠራዊቱ ዘንድ የሚከናወኑ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ለውጦችን በተመለከተም ምዘና አድርገዋል።

በዚህ ወቅትም የመከላከያ ሠራዊት አመራር እና አባላት ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም አባላቱ ያላቸውን ሁሉ ለሀገራቸው ለመስጠት ቆራጥ እንደሆኑ መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.