Fana: At a Speed of Life!

በስጋ ደዌ ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳሳካዋ የጤና ፋውንዴሽን እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በስጋ ደዌ ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

መሰረቱን በጃፓን ያደረገው ሳሳካዋ የጤና ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ታካሂሮ ናንሪ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፥ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ በስጋ ደዌ ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውንና ለተለያዩ የጤና እክል የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በትምህርት፣ በጤና እንዲሁም በገቢ ማስገኛ ዘርፎች እየሰራ ነው፡፡

ለአብነትም ፋውንዴሽኑ ለኢትዮጵያ ስጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሔራዊ ማኅበር የስጋ ደዌ ተጠቂ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የገቢ ማስገኛ እንዲሆን ባለ አምስት ወለል ሕንጻ ማሰራቱን ገልጸዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በሚኒስቴር መ/ቤቱ በኩል የአካል ጉዳት ጉዳይ በሁሉም መስክ ተካቶ ሁሉ አቀፍ ለውጥ እንዲመጣ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው ፥ በስጋ ደዌ ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍ በፋውንዴሽኑ በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረትም አድንቀዋል፡፡

የስጋ ደዌ ተጠቂዎችን ለመደገፍና በአካል ጉዳት ላይ በትበብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.