Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ክልል ሕዝብን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ  

አዲስ አበባ፣ሰኔ 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽነትና የተጠቃሚውን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በደቡብ ምዕራብ ክልል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪጅን ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ መርሐ ግብር ዛሬ ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ለክልሉ ሕዝብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ዛሬ የተዋቀረው ክልላዊ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሪጅን ጽሕፈት ቤቱ መቋቋምም በዘርፉ ያለውን ችግር ለመፍታትና የተጠቃሚውን ቁጥር ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንደገለጹት÷ እየጨመረ የመጣው የኤሌክትሪክ ፍላጎት ካልተመለሰ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም፡፡

በክልሉ የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ ችግር በፍጥነት ለመፍታት በቅንጅት እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡

የተዋቀረው አዲሱ ክልላዊ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪጅን ጽሕፈት ቤት ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራውን ይጀምራል የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.