በእናቶች እና ሕጻናት የስነ ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ የሚያተኩር ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእናቶች እና ሕጻናት የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ የሚያተኩር የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
መድረኩ የተዘጋጀው በፒ.ኤም.ኤ ኢትዮጵያ ሲሆን÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ጆን ሆፕኪንስ ስኩል ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ ዩኒቨርሲቲ በእናቶች እና ሕጻናት የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ የጥናት ውጤቶችን ለጤና ሚኒስቴርና ለሌሎች አጋር አካላት አቅርበዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በዚሁ ወቅት አንደገለጹት÷ተቋማት በእቅድ ዝግጅታቸው ላይ የተገኙትን የጥናት ውጤቶች እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም አለባቸው፡፡
ጥናቶቹ ለሀገራዊ እቅዶችና ውሳኔ አሰጣጦች ግብዓት የሚሆኑ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎት አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸውም ብለዋል፡፡
ጥናቶቹ የእናቶች እና ሕጻናት ጤና ላይ ትኩረት ማድረጋቸው መልካም መሆኑን ጠቅሰው÷ የቤተሰብ እቅድ ላይ የተሰራው ስራ ውጤታማ እንደነበርም አመላክተዋል።
በክልሎች መሃል የሚታየውን ልዩነት ማጥበብ፣ ለእናቶች የሚሰጠውን የማማከር አገልግሎት ማሻሻል እና ቀጣይነት ያለው የጤና እንክብካቤ ላይ በስፋት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የቀረቡ ጥናቶች ተግባራዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚረዱ የገለጹት ደግሞ የጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ህጻናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም ናቸው፡፡
በጥናቶቹ መሰረት የቤተሰብ ምጣኔ አጠቃቀም የተሻለ ለውጥ ማሳየቱ አበረታች ነው መባሉን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!