በማልታ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሳተፍ እንሻለን አሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማልታ የሚገኙ እና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እየሰሩ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
በማልታ የንግድ ምክር ቤት በተዘጋጀ bኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ የተመራው ልዑክ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ በኩል በዝርዝር ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳንዶካን ደበበ ደግሞ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ ስለተዘረጉ መሰረተ ልማቶች እና ለአምራቾች ስለቀረቡ ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎች ገለፃ ማድረጋቸውን ነው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
በመድረኩ ተሳታፊ ከነበሩ አምራች ኩባንያዎች መካከል ኤፒ ቫሌታ፣ አኩዋ ባዮ ቴክ ግሩፕ፣ ኮሪንቲሀ ግሩፕ፣ ትረስት ስታምፕ እና ሳልቮ ግርማ ሎጀስቲክስ ግሩፕ የተሰኙት በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለጹት።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!