በኦስትሪያ በበረዶ ናዳ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦስትሪያ አልፕስ ተራሮች በደረሰ የበረዶ ናዳ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።
ሰዎቹ በወቅቱ የበረዶ ሽርሽር እያደረጉ ነበር ተብሏል።
አደጋው በሁለት የተለያዩ ቦታዎች መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።
ከሳልዝበርግ በስተደቡብ ምስራቅ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዳቺስቴየን አካባቢ በደረሰው አደጋ 5 የቼክ ሪፐብሊክ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው።
በሌላ በኩል ካሪንቲያ በተባለው አካባቢ በደረሰው አደጋ ደግሞ የ33 ዓመት የፖሊስ መኮንን ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።
በናዳው የተጎዱ ዜጎችን ለማፈላለግ የነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ ስፍራው ተሰማርተዋል።
ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision