Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ክልል 50 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና ይወስዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ክልል በ2014 ዓ.ም በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ከ49 ሺህ 883 በላይ ተማሪዎች ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፥ ፈተናው ከመጪው ሰኔ 28 እስከ 30 ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥ ጠቁመው÷ በ1 ሺህ 77 ትምህርት ቤቶች በ1 ሺህ 69 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከ49 ሺህ 883 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡ ለዚህም 2 ሺህ 194 ፈታኞች መዘጋጃታቸውን ነው የገለጹት፡፡
የፈተና ሂደቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የትምህርት መዋቅሩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የጸጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ተፈታኞች ከስርቆትና ከኩራጃ በፀዳ ሁኔታ እንዲፈተኑ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.