የሀገር ውስጥ ዜና

በአምባሰል ወረዳ 16 የሞርታር ተተኳሽ ተያዘ

By Meseret Awoke

July 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ 02 ቀበሌ 16 የሞርታር ተተኳሽ ለሦስተኛ ጊዜ መያዙን የወረዳው ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት የሰው ኃይል አደረጃጀት የፀጥታ ስምሪት ቡድን መሪ አቶ አንተነህ ኃይሌ እንደገለፁት ፥ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ነው የሞርታር ተተኳሹ የተያዘው።

የሞርታር ቅንቡላው ግለሰብ ቤት ተከዝኖ በዛሬው እለት ላይ መያዙን የገለጹት አቶ አንተነህ ፥ የተገኘው የሞርታር ቅንቡላ አሸባሪው ህወሓት ከአካባቢው ሸሽቶ ሲሄድ ጥሎት የሄደው ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።

አክለውም በአካባቢው የአሰሳ ስራው ተጠክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።

ዛሬ የተያዘው የሞርታር ቅንቡላ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑንና ከዚህ በፊት በዚሁ ቀበሌ 28 የሞርታር ተተኳሽ መያዙን መግለጻቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!