የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አቀረቡ

By Meseret Awoke

July 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አቀረቡ።

አምባሳደሩ በዚህ ወቅት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ አምባሳደር ሞሊ ፊ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ባዘጋጁት መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!