Fana: At a Speed of Life!

ለፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብ 10 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብ 10 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ።
ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብ ዛሬ ጎንደር ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ÷ ክለቡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል ብለዋል።
ክለቡ በውድድር ዘመኑ ላስመዘገበው ውጤት የከተማ አስተዳደሩ 7 ሚሊየን 462 ሺህ 500 ብር፣ ከክለቡ 2 ሚሊየን 487 ሺህ 500ብር በድምሩ 9 ሚሊየን 950 ሺህ 500 ብር ለክለቡ ተጫዋቾችና ለአሰልጣኞች እንዲሁም ለአጠቃላይ ሰራተኞችና የቦርድ አመራሮች የማበረታች ሽልማት ተበርክቷል።
በ2015 የውድድር ዘመን ክለቡ የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግብም ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡
ለክለቡ ስኬታማ ጉዞ በገንዘብና በሞራል ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና ቀርቧል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.