Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ሩሲያ ከሚገቡበት በፒተርስበርግ ከተማ ከሚገኘው የወደብ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መከሩ፡፡

በአምባሳደሩ የተመራ ልዑክ የሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ኢካተርኢና ለቤዴቫ ጋር በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ነው የመከሩት።

በተለይም በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የሚገኘው ወደብ የኢትዮጵያ ምርቶች የሚገቡበት እንደመሆኑ በአካባቢው ከሚገኙ የንግድ ኩባንያዎች ላኪዎች ትስስር የሚፈጥሩበትን መንገድ ለማመቻቸት በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነስቷል።

በተመሳሳይ በዕለቱ በአካባቢው ያለውን የሎጅስቲክ አገልግሎት በተመለከተ ሃላፊዎቹ እንደመከሩበት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.