Fana: At a Speed of Life!

ክልሎች ያዘዙትን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው የአሰራር ችግር ፈጥሮብኛል -የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ሰኔ 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ክልሎች ያዘዙትን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው የአሰራር ችግር ፈጥሮብኛል ሲል የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ገለፀ።

የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዳሬክተር አቶ ስለሞን አምባቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ክልሎች እንዲመረት ያዘዙትን የተሽከርካሪ ስሌዳ ተገቢውን ክፍያ ከፍለው እንዲውስዱ እና ለተጠቃሚው እንዲያደርሱ  አሳስበዋል።

በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች የማተምና የማሰራጨት ስራን የሚያከናውነው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በጊዜያዊነት ተፈጥሮ የነበረው የምርት እጥረት ቀርፎ ወደ ስራ መግባቱን አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜም ለክልልና ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮዎች በፈለጉት አይነትና መጠን የተሽከርካሪ ሰሌዳዎችን አምርቶ በማከፋፈል ላይ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

በተቃራኒውም በተለይ ክልሎች አዘው ያስመረቱትን ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው ለአሰራር ችግር እየፈጠረባቸው እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

ክልሎች ያስመረቱትን ሰሌዳ አስፈላጊውን ክፍያ ከፍለው እንዲወስዱና ለተጠቃሚው እንዲያደርሱ ያሳሰቡት ዳይሬክተሩ ÷ በቀጣይ መሠል ችግሮች እንዳያጋጥሙ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.