Fana: At a Speed of Life!

ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ዱቄት እና ሊጥ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ 36 ኩንታል ዱቄት እና 25 በርሜል ሊጥ ተያዘ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ጎሮ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከባዕድ ነገር ጋር ተተቀላቅሎ የተዘጋጀ የጤፍ ዱቄትና እንጀራ ተይዟል።

በወቅቱም 36 ኩንታል ዱቄት እና 25 በርሜል ሊጥ፣ 300 የተጋገረ እንጀራ እንዲሁም ለእንጀራ መጋገሪያ ሲያገለግሉ የነበሩ 9 የእንጀራ

ምጣዶችና ሌሎች ግብዓቶችን መያዙን የወረዳው አስተዳደር የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ውብነህ ዋሴ ተናግረዋል።

ድርጊቱን ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የሙያ ማረጋገጫ የሌላቸው ናቸው ተብሏል።

ማህበረሰቡ ቤት በሚያከራይበት ጊዜ የግለሰቦችን መረጃ በአግባቡ በመያዝና ለምን ተግባር እንደሚውል ማወቅና ክትትል ማድረግ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ችግሩ በአንድና በሁለት አካላት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት ጥቆማና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.