ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊስ ኦልብራይት ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያና በዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት መካከል የተፈጠረው ጠንካራ አጋርነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።
የዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊስ ኦልብራይት በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ህጻናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ የምታደርገው እንቅስቃሴ ምሳሌ እንደሚሆን መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዓለም አቀፍ አጋርነት የትምህርት ልዑካን ቡድን ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።
ልዑኩ ከትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ጋር የተወያየ ሲሆን፥ በቀጣይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ከዓለም ባንክ ተወካዮች ጋር እንደሚወያይ ይጠበቃል።
ዓለም አቀፍ አጋርነት ለትምህርት ሃብት በማሰባሰብ ለኢትዮጵያና ለሌሎች ታዳጊ ሃገራት በትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision