የሀገር ውስጥ ዜና

ኮይካ ለጤና ሚኒስቴር 31 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

By Melaku Gedif

July 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለጤና ሚኒስቴር 31 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኮይካ ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ የተገዙት የህክምና ቁሳቁሶቹ የእናቶችና የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ እና ጤናቸው ለማሻሻል የሚያግዙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ድጋፉን የጤና ሚኒስትር ዶክት ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለትመረከባቸውን ከዩኒሴፍ በኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የህክምና ቁሳቁሶቹ ለአፋርና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የሚሰራጩ መሆኑ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡