Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ባላለሙ አካላት ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ባላለሙ አካላት ላይ በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ የሐረሪ ክልል ካቢኔ አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡
የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) በ2014 ዓ.ም የሴክተር መስሪያ ቤቶች ዕቅድ ክንውን እና በ2015 በጀት ዓመት አማራጭ የበጀት ድልድል ላይ ተወያይቷል።
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግግር በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ባላለሙ አካላት ላይም በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸዋል፡፡
በተለይም በክልሉ የሕግ የበላይነትን ከማጎልበትና ሰላምን ከማጠናከር አንፃርም ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የገለጹት አቶ ኦርዲን÷ በቀጣይም በላቀ ቁርጠኝነት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲቀረፉና ሕዝቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የ2015 በጀት ዓመት የበጀት ዝግጅት የህብረተሰቡን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል ተግባራት ላይ ትኩረቱን ሊያደርግ ይገባል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.