Fana: At a Speed of Life!

እስራኤልና ግብፅ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ አውሮፓ ኅብረት መላክ የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል እና ግብፅ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡

ሀገራቱ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ አውሮፓ ለመላክ ከኅብረቱ ጋር ሥምምነት ላይ የደረሱት ከሩሲያ የሚያስገቡት የጋዝ ምርት መቆሙን ተከትሎ ባጋጠማቸው የኃይል እጥረት መሆኑን ሲጂ ቲ ኤን አመላክቷል፡፡

የእስራኤል የኃይል ሚኒስትር ካሪን ኤልሃራር፥ የሥምምነቱ መፈረም እስራኤል በኃይል አቅርቦት ገበያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ሚና የሚያሳድግ ነው ብለዋል።

እስራኤል በባሕር የተፈጥሮ ጋዝ ምርቱን ወደ አውሮፓ እንደምትልክም ነው የተመለከተው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ኃላፊ ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን፣ የግብፅ ነዳጅ ሚኒስትር ታሬክ ኤል ሞላ እንዲሁም የእስራኤል ኢነርጂ ሚኒስትር ካሪን ኤልሃራር የሦስትዮሽ ሥምምነቱን ፈርመዋል፡፡

ቮን ደር ሌየን ኮሚሽኑን ወክለው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ሥምምነቱ ኅብረቱ በሩሲያ ላይ ካለው ጥገኝነት ነጻ እንዲወጣ ይረዳል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.