Fana: At a Speed of Life!

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሙሀመድ አብዲከር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በነበራቸው ውይይት  በቀጠናው የክህሎት ልማት እና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የሰራተኞች ተዘዋውሮ የመስራት፣ የዜጎችን ሰብዓዊ እና ማህበራዊ መብቶችን ማስጠበቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከዳይሬክተሩ ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ የሚኒስትሮች ፎረምን የምትመራ ሀገር እንደመሆኗ ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታን በተመለከተም ውይይት ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

ከቀጠናው ባለፈ ከሌሎች ሀገራት እና አህጉራት ጋር ህጋዊ የሆነ የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ዝውውር ሥርዓት መዘርጋት እና በትብብር ለመስራት በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርጅቱ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጡንም አብራርተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.